የዳሰሳ ጥናት፦ አረጋውያን የጤና አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ ያላቸው ተሞክሮ

Caution: JavaScript execution is disabled in your browser or for this website. You may not be able to answer all questions in this survey. Please, verify your browser parameters.

ለአረጋውያን ስለሚሰጡ ጥራት ያላቸው የጤና አገልግሎቶች በዚህ የዓለም ጤና ድርጅት የዳሰሳ ጥናት ላይ ለመሳተፍ እንኳን ደህና መጡ። ለተሳትፎዎ እናመሰግናለን።

ምላሾችዎ ለአረጋውያን የሚሰጡ ጥራት ያላቸው የጤናና የእንክብካቤ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ለማዘጋጀት ይረዳሉ።

መግቢያ

በዓለም ዙሪያ ሰዎች ከበፊቱ የበለጠ ዕድሜ እየኖሩ ነው። ስለዚህ በእርጅና ወቅት የምንፈልጋቸው የጤና አገልግሎቶች ከመቼውም በላይ አስፈላጊ ሆነዋል። እነዚህ ለምሳሌ የቤተሰብ ሐኪምን፣ ጤና ጣቢያን ወይም ክሊኒክን በመደበኛነት መጎብኘት፣ ከፋርማሲ መድኃኒት ማግኘት፣ በሆስፒታል የልዩ ሕክምና አገልግሎት ማግኘት፣ የመልሶ ማቋቋም ወይም የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች፣ በቀን እንክብካቤ ማዕከል የሚሰጥ እንክብካቤ፣ እንዲሁም በቤት ወይም መኖሪያ ባለው ተቋም የረጅም ጊዜ እንክብካቤና በዕለት ተዕለት ኑሮ የሚሰጥ እገዛን ያካትታሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት የአረጋውያንን የተለያዩ ፍላጎቶች ለማሟላት ለእነዚህ አገልግሎቶች አዳዲስ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ለማዘጋጀት ከአገሮች ጋር እየሠራ ነው። ዓላማው አገልግሎቶቹን የተሻሉ፣ ደህንነት ያላቸውና አክብሮት የሚያሳዩ ማድረግ ነው፤ ይህም ግቦችዎን፣ እሴቶችዎንና ምርጫዎችዎን ያገናዝባል።

ይህን በጥሩ ሁኔታ ለማድረግ መጀመሪያ እነዚህን አገልግሎቶች በየቀኑ የሚጠቀሙ ሰዎችን መስማት አለብን።

የጤና አገልግሎቶችን የመጠቀም ተሞክሮዎ ለእኛ አስፈላጊ ነው።

እውነተኛ ተሞክሮዎን ማወቅ እንፈልጋለን፦ ምን በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዳለ፣ ምን አስቸጋሪ እንደነበር፣ እና የጤና አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ ምን እንዲለወጥ እንደሚፈልጉ ማወቅ እንፈልጋለን።

ይህ የዳሰሳ ጥናት ስለ ምንድን ነው?

አረጋውያን የጤና አገልግሎቶችን እንዴት እንደሚያገኙ መረዳት እንፈልጋለን። ይህም ያጋጠሙዎትን ችግሮች፣ ያገኙትን ወይም ያላገኙትን ድጋፍ፣ እና ሊሻሻል ይገባል ብለው የሚያስቡትን ያካትታል። ምላሾችዎ ለአረጋውያን ጥራት ያላቸው የጤና አገልግሎቶች የወደፊት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ለማዘጋጀት ይረዳሉ። መመዘኛዎቹም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ሰዎች ቅድሚያ በሚሰጧቸው ነገሮች ላይ እንዲመሠረቱ ይረዳሉ።

በሚችሉት መጠን ብዙ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ በአክብሮት እንጋብዝዎታለን። ትክክለኛ ወይም የተሳሳተ ምላሽ የለም።

ማን መሳተፍ ይችላል?

ለመሳተፍ የሚከተሉትን ሁለቱንም መስፈርቶች ማሟላት አለብዎት፦

ዕድሜዎ 60 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መሆን

እና

ባለፉት 12 ወራት ቢያንስ አንድ ጊዜ የጤና አገልግሎት መጠቀም፣ ለምሳሌ ወደ ክሊኒክ፣ ሆስፒታል ወይም የቀን እንክብካቤ ማዕከል መሄድ።

ከፈለጉ የሚያምኑትን ሰው፣ ለምሳሌ የቤተሰብ አባል፣ ጓደኛ፣ የማህበረሰብ አባል ወይም የጤናና የእንክብካቤ ሠራተኛ፣ ጥናቱን ለመሙላት እንዲረዳዎት መጠየቅ ይችላሉ።

ተሳትፎዎ

ተሳትፎዎ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። ለመሳተፍ ስለ ጥናቱ የተሰጠውን መረጃ መረዳትና ካሉት ቋንቋዎች በአንዱ መጠይቁን መሙላት መቻል አለብዎት።

ምላሾችዎን ከመላክዎ በፊት በማንኛውም ጊዜ ምክንያት ሳይሰጡ ከጥናቱ መውጣት ይችላሉ። ምላሾችዎ ማንነትዎ ሳይታወቅ ይሰበሰባሉ፣ በሚስጥርም ይያዛሉ።

ማንነትዎን የሚያሳይ መረጃ፣ ለምሳሌ ስም፣ የአባት ስም ወይም የኢሜይል አድራሻ፣ አንሰበስብም። ስለዚህ ከላኩ በኋላ የእርስዎን ምላሾች ለይተን ማግኘት አንችልም። ይህም ጥናቱን ከላኩ በኋላ ምላሾችዎን መሰረዝ አንችልም ማለት ነው።

ጥናቱን ሲልኩ ከላይ ያለውን መረጃ እንዳነበቡና እንደተረዱ ያረጋግጣሉ፣ በዚህ ጥናት ለመሳተፍና መረጃዎ ለተገለጹት ዓላማዎች እንዲሰበሰብና እንዲቀናበር መፍቀድዎን ያረጋግጣሉ።

ይህን መጠይቅ በአረጋዊ ሰው ስም እየሞሉ ከሆነ፣ የዚያን ሰው ግላዊነት ማክበር እና የግል መረጃውንና ምላሾቹን በሚስጥር መጠበቅ አለብዎት።

ጥያቄ ካለዎት ወይም ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ባለሙያ የሆኑትን ዶ/ር ዩካ ሱሚን በኢሜይል ያነጋግሩ፦ sumiy@who.int።

በኮከብ ምልክት (*) የተመለከቱ ጥያቄዎች ግዴታ ናቸው፤ ለመቀጠል መመለስ አለብዎት። ሌሎቹን ጥያቄዎች በተቻለ መጠን ሙሉና ትክክለኛ ምላሽ እንዲሰጡ እናበረታታዎታለን። አንድ ጥያቄ ሳይመልሱ ከቀሩ፣ «ቀጣይ» ወይም «አስገባ» ሲመርጡ ማስታወሻ ይታያል፤ ሆኖም ሳይመልሱ መቀጠል ይችላሉ። በተለያዩ ቦታዎች ስለ ጤናና እንክብካቤ አገልግሎቶች የአረጋውያንን ፍላጎቶች፣ ተሞክሮዎችና አመለካከቶች ለመረዳት በሁሉም ክፍሎች የሚሰጡት ምላሽ አስፈላጊ ነው።

ጥናቱን ለመሙላት በግምት 30 ደቂቃ ይወስዳል፣ ነገር ግን የሚወስደው ጊዜ ከሰው ወደ ሰው ሊለያይ ይችላል።

ለሰጡን ጊዜና ላሳዩን እምነት ከልብ እናመሰግናለን።

There are 69 questions in this survey.