ለአረጋውያን የሚሰጥ ጤናና እንክብካቤ አገልግሎት ጥራት በተመለከተ ለጤና እንክብካቤ አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች እና የስራ ሃላፊዎች/አስተዳዳሪዎች የተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት

Caution: JavaScript execution is disabled in your browser or for this website. You may not be able to answer all questions in this survey. Please, verify your browser parameters.

መግቢያ እና በዳሰሳ ጥናቱ የመሳተፍ ፈቃድ መቀበያ

ለአረጋውያን የሚሰጥ ጤናና እንክብካቤ አገልግሎት ጥራት በተመለከተ በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሚካሄደው በዚህ ዳሰሳ ጥናት ላይ ለመሳተፍና አስተዋጽኦ ለማድረግ ስለፈለጉ እናመሰግናለን። በዳሰሳ ጥናቱ ለመሳተፍ እንኳን ደህና መጡ።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ለአረጋውያን የሚሰጥ ጤና አገልግሎትና እንክብካቤ ጥራትን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን እያዘጋጀ ነው። ይህ ጥናት፣ የፕሮግራም የስራ ሃላፊዎች/አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ፣ የጤናና የእንክብካቤ ሰጪ ሠራተኞች ለአረጋውያን ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ምን ነገሮች አስፈላጊ እንደሆኑና ይህን ለማሳካት ምን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ለመረዳት ያለመ ነው።

ጤናና እንክብካቤ አገልግሎት ጥራት ስንል፣ ውጤታማ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ግለሰቡን ማዕከል ያደረገ፣ በወቅቱ የሚሰጥ፣ ፍትሐዊ፣ የተቀናጀና ሀብትን በብቃት የሚጠቀም እንክብካቤ ማለታችን ነው። በተሞክሮዎ መሠረት ምን ጥሩ ሁኔታ እየተሠራ እንደሆነ፣ ምን ችግሮች እንደሚያጋጥሙዎትና ለአረጋውያን የሚሰጠውን ጤናና እንክብካቤ አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ምን ለውጦች እንደሚረዱ ማወቅ እንፈልጋለን። አስተያየትዎ ወደፊት ለአረጋውያን ጥራት ያለው ጤናና እንክብካቤ አገልግሎት የሚያግዙ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ለማዘጋጀት ይረዳል።

በዳሰሳ ጥናቱ ማን መሳተፍ ይችላል?

የሚከተሉትን መስፈርቶች ካሟሉ መሳተፍ ይችላሉ፦

  • ዕድሜያቸው 60 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ አረጋውያን የጤና እና/ወይም የእንክብካቤ አገልግሎቶችን የሚሰጡ፣ የሚያስተዳድሩ ወይም የሚያደራጁ የጤና ወይም የእንክብካቤ አገልግሎት ሰጪ ሠራተኛ፣ ወይም የጤና ፕሮግራም አስተዳዳሪ ከሆኑ፤ እና
  • የጥናቱን መረጃዎች መረዳትና ከቀረቡት ቋንቋዎች በአንዱ መጠይቁን መሙላት ከቻሉ።

መጠይቁን ለመሙላት በግምት 30–35 ደቂቃ ይወስዳል። 

አብዛኞቹ ጥያቄዎች ለአረጋውያን ጥራት ያለው የጤና ወይም እንክብካቤ አገልግሎት ለመስጠት ምን መኖር እንዳለበት ይጠይቃሉ፤ ጥቂቶቹ ጥያቄዎች ግን የእርስዎን ተሞክሮ ወይም ስለሚሠሩበት የሥራ አካባቢ የሚመለከቱ ናቸው። በመጠይቁ የኮከብ ምልክት (*) ያለባቸው ጥያቄዎች የግድ መመለስ ያለባቸው ሲሆኑ ሌሎቹ ጥያቄዎች ደግሞ በተቻለዎት መጠን ትክክለኛ መልስ እንዲሰጡ እናበረታታዎታለን። ከእነዚህ ጥያቄዎች አንዱን ሳይመልሱ «ቀጣይ» ወይም «አስገባ» ሲጫኑ የማስታወሻ መልዕክት ይታየዎታል፤ ነገር ግን ጥያቄውን ሳይመልሱ መቀጠል ይችላሉ።

በሁሉም የጥናቱ ክፍሎች የሚሰጧቸው መልሶች በተለያዩ የሥራ አካባቢዎች የሚሠሩ የጤናና የእንክብካቤ ሠራተኞችን ፍላጎት፣ ተሞክሮና አመለካከት እንድንረዳ ይረዳሉ።

የእርስዎ ተሳትፎ በተመለከተ

ተሳትፎ በፈቃደኝነት ነው። መልሶችዎ ማንነትዎን አይገልጹም፣ በሚስጥርም ይጠበቃሉ። ትክክል ወይም ስህተት የሚባል መልስ የለም።

መልሶችዎን ከማስገባትዎ በፊት በማንኛውም ጊዜ ከጥናቱ መውጣት ይችላሉ። ማንነትዎን የሚለይ መረጃ ስለማንሰበስብ፣ መጠይቁን ከተጠናቀቀ በኋላ መልሶችዎን ፈልገን ማግኘት ወይም መሰረዝ አንችልም።

መጠይቁን ሞልተው በመላክ ከላይ ያለውን መረጃ እንዳነበቡና እንደተረዱ፣ በፈቃደኝነት ለመሳተፍ እና መልሶችዎ ለተገለጹት ዓላማዎች እንዲሰበሰቡና እንዲተነተኑ መስማማትዎን ያረጋግጣሉ።

ጥያቄ ካለዎት፣ የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ኦፊሰር ዶ/ር ዩካ ሱሚን በዚህ ኢሜይል ያነጋግሩ፦ sumiy@who.int።

ለፈቃደኝነትዎና ላደረጉት አስተዋጽኦ ከልብ እናመሰግናለን።

There are 93 questions in this survey.