የእንኳን ደህና መጡ መልእክት
ለአረጋውያን ስለሚሰጡ ጥራት ያላቸው የጤና አገልግሎቶችና ያለ ክፍያ እንክብካቤ ሰጪዎች ተሞክሮ በዚህ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ጥናት ላይ ለመሳተፍ እንኳን ደህና መጡ። እናመሰግናለን።
ምላሾችዎ ለአረጋውያን ጥራት ያላቸው የጤናና የእንክብካቤ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ለማዘጋጀት ይረዳሉ።
መግቢያ
በዓለም ዙሪያ ሰዎች ከበፊቱ የበለጠ ዕድሜ እየኖሩ ነው። ስለዚህ በእርጅና ወቅት የምንፈልጋቸው የጤና አገልግሎቶች የበለጠ አስፈላጊ ናቸው። ለምሳሌ የቤተሰብ ሐኪምን በመደበኛነት መጎብኘት፣ ከፋርማሲ መድኃኒት ማግኘት፣ በሆስፒታል የልዩ ሕክምና አገልግሎት፣ እና በቤት የዕለት ተዕለት እንክብካቤና እገዛ፣ እንደ የረጅም ጊዜ እንክብካቤ።
የዓለም ጤና ድርጅት የአረጋውያንን የተለያዩ ፍላጎቶች ለማሟላት አዳዲስ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ከአገሮች ጋር ያዘጋጃል። ዓላማው አገልግሎቶቹን የተሻሉ፣ ደህንነት ያላቸውና አክብሮት የሚያሳዩ ማድረግ ነው፣ ግቦችዎን፣ እሴቶችዎንና ምርጫዎችዎን በማገናዘብ።
ይህን በጥሩ ሁኔታ ለማድረግ መጀመሪያ አገልግሎቶቹን በየቀኑ የሚጠቀሙ ሰዎችን መስማት አለብን።
የሚወዱትን ሰው መንከባከብ ጥልቅ ትርጉም ሊኖረው ይችላል፣ ግን አድካሚ፣ ብቸኝነት የሚያስከትልና በስሜት፣ በአካልና በገንዘብ ከባድ ሊሆን ይችላል። ብዙ እንክብካቤ ሰጪዎች የራሳቸውን ጤና፣ ሥራና ቤተሰብ እያስተዳደሩ ብዙ ጊዜ የማይታይ ከባድ ሸክም ይሸከማሉ። ድምጽዎ አስፈላጊ ነው። ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቢኖርዎት ተሞክሮዎን ማካፈል ወደፊት እንዲታወቁ፣ እንዲደመጡና የተሻለ ድጋፍ እንዲያገኙ ይረዳል።
የጤና አገልግሎቶችን የመጠቀም ተሞክሮዎ ለእኛ አስፈላጊ ነው።
ያለ ክፍያ እንክብካቤ ሰጪ እንደመሆንዎ እውነተኛ ተሞክሮዎን፣ ምን ጥሩ እንደነበር፣ ምን አስቸጋሪ እንደነበርና ምን እንዲለወጥ እንደሚፈልጉ ማወቅ እንፈልጋለን።
ይህ ጥናት ስለ ምን ነው?
አረጋውያን እና ያለክፍያ እንክብካቤ የሚሰጧቸው ሰዎች የጤና አገልግሎትን ሲያገኙ ያላቸውን ተሞክሮ መረዳት እንፈልጋለን። በተለይም በጤና አገልግሎት ሲጠቀሙ ያጋጠሟቸውን ችግሮች፣ ያገኙትን ወይም ያላገኙትን ድጋፍ፣ እንዲሁም እንዲሻሻል የሚፈልጉትን ነገር ማወቅ እንፈልጋለን።
የሚያካፍሉት ሀሳብና ተሞክሮ ለወደፊቱ ለአረጋውያን የሚሰጡ ጥራት ያላቸው የጤና አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲዘጋጁ ጠቃሚ ግብዓት ይሆናል። በዚህም የጤና አገልግሎቶቹ ከአረጋውያንና እነሱን ከሚንከባከቡ ሰዎች ፍላጎት በመነሳት እንዲሻሻሉ ይረዳል።
በሚችሉት መጠን ብዙ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ እናበረታታዎታለን። የተሳሳተ የሚባል ምላሽ የለም።
በዚህ ጥናት ለመሳተፍ የሚከተሉትን ሁለቱንም መስፈርቶች ማሟላት ያስፈልጋል፦
1. ዕድሜዎ 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መሆን አለበት፤ እንዲሁም ዕድሜያቸው 60 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ያለምንም ክፍያ እንክብካቤ የሚሰጡ መሆን አለብዎት። ይህ የቤተሰብ አባል፣ ጓደኛ ወይም የማኅበረሰብ አባል ሊሆን ይችላል። በአሁኑ ጊዜ እንክብካቤ እየሰጡ ያሉ ወይም ባለፉት 12 ወራት ውስጥ እንክብካቤ ሰጥተው የሚያውቁ መሆን አለበት። ለሚሰጡት እንክብካቤም የገንዘብ ክፍያ ተቀብለው የማያውቁ መሆን አለበት።
2. እንክብካቤ የሚሰጡት ሰው ዕድሜው 60 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነና ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ የጤና አገልግሎት ተጠቅሞ የሚያውቅ መሆን አለበት። ማለትም ወደ ጤና ጣቢያ፣ ሆስፒታል ወይም የቀን እንክብካቤ ማዕከል የሄደ መሆን አለበት።
መጠይቁን ለመሙላት እርዳታ ከፈለጉ፣ የሚያምኑትን ሰው—ለምሳሌ የቤተሰብ አባል፣ ጓደኛ፣ የማኅበረሰብ አባል ወይም የጤናና የእንክብካቤ ባለሙያ—እንዲረዳዎት መጠየቅ ይችላሉ።
ተሳትፎዎ
ተሳትፎ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የጥናቱን መረጃ በአግባቡ በመረዳትና መጠይቁን ከቀረቡት ቋንቋዎች በአንዱ መሙላት መቻል አለብዎት።
መልሶችዎን ከመላክዎ በፊት በማንኛውም ጊዜ ምክንያትዎን ሳይገልጹ ከጥናቱ መውጣት ይችላሉ። የሚሰጡት መልሶች ማንነትዎን በማይገልጽ መንገድ የሚሰበሰቡ ሲሆን፣ በሚስጥር ይያዛሉ።
ስምዎን ወይም የአባትዎን ስም እንደዚሁም የኢሜይል አድራሻዎን ለይቶ ሊያሳውቅ የሚችል ሌላ መረጃ ስለማንሰበስብ፣ መልሶችዎን ካስገቡ በኋላ ከእርስዎ ጋር ለማዛመድ ወይም መልሰን ለማግኘት አንችልም። ስለዚህ መጠይቁን ካስገቡ በኋላ መልሶችዎን ማስወገድ አንችልም።
መጠይቁን ሲልኩ፣ ከላይ የቀረበውን መረጃ አንብበው እንደተረዱት፣ በፈቃደኝነት በዚህ ጥናት ለመሳተፍ እንደተስማሙ እና ለተገለጸው የጥናት ዓላማ መረጃዎ እንዲሰበሰብና በተገቢው መንገድ እንዲሠራበት ፈቃደኛ መሆንዎን ያረጋግጣሉ።
ይህን መጠይቅ ያለ ክፍያ እንክብካቤ በሚሰጥ ሰው ስም እየሞሉ ከሆነ፣ የዚያን ሰው ግላዊነት ማክበር እና የግል መረጃውንና ምላሾቹን በሚስጥር መጠበቅ አለብዎት።
ጥያቄ ካለዎት ወይም ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ተጠሪ ለሆኑት ዶ/ር ዩካ ሱሚ ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ፦ sumiy@who.int።
በኮከብ (*) ምልክት የተለዩ ጥያቄዎች የግድ መመለስ ያለባቸው ሲሆን፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለመቀጠል እነዚህን መመለስ ያስፈልጋል። ለሌሎቹ ጥያቄዎች ግን በተቻለዎት መጠን ሙሉና ትክክለኛ መልስ እንዲሰጡ እናበረታታዎታለን።
ከእነዚህ ጥያቄዎች ማንኛውንም ሳይመልሱ ከተዉት፣ “ቀጣይ” (Next) ወይም “አስገባ” (Submit) የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄውን እንዲመልሱ የሚያስታውስ መልዕክት ይታያል። ሆኖም፣ ሳይመልሱ መቀጠል ይችላሉ።
በመጠይቁ ሁሉም ክፍሎች የሚሰጡት መልሶች በተለያዩ የጤናና የእንክብካቤ አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ያለክፍያ እንክብካቤ ሰጪዎችና የአረጋውያን ፍላጎቶችን፣ ተሞክሮዎችንና አመለካከቶችን በተሻለ ሁኔታ እንድንረዳ ጠቃሚ ናቸው።
ጥናቱ በግምት ከ30 እስከ 35 ደቂቃ ይወስዳል።
ለጊዜዎና ላሳዩን እምነት ከልብ እናመሰግናለን።
There are 82 questions in this survey.